Fana: At a Speed of Life!

የሠራዊት አመራሮች ሀብት የማሣወቅ እና የመመዝገብ ስራ እየተከናወነ ይገኛል

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሠራዊት አመራሮች ሀብት የማሣወቅ እና የመመዝገብ ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝ የመከላከያ ሥነ ምግባር መከታተያ ዳይሬክቶሬት አስታወቀ፡፡

የዳይሬክቶሬቱ ተወካይ ሌተናል ኮሎኔል ሀይሉ አሠፋ ዳይሬክቶሬቱ ጉዳዩ የሚመለከታቸውን የሠራዊት አመራሮች እየመዘገበ እንደሚገኝ ነው የተናገሩት፡፡

ለዳይሬክቶሬቱ ሙያተኞች በጦር ክፍሎች በመዘዋወር የግንዛቤ ማሥጨበጫ ስልጠና መሰጠቱንም ተናግረዋል።

ሙስናን የሚፀየፍ ብልሹ አሠራርን የሚኮንን እና የሚታገል ዜጋ ለመፍጠር የሀብት ምዝገባ እና ማሣወቅ አንዱ መንገድ ነው ብለዋል፡፡

በየደረጃው የሚገኙ የመከላከያ ሥነ ምግባር መከታተያ መኮንኖች በዚሁ እና በሌሎች ሥነ ምግባር ተኮር ሥራዎች ላይ ተገቢውን እንቅስቃሴ እያደረጉ እንደሚገኙም አብራርተዋል።

በዳይሬክቶሬቱ የሀብት ምዝገባ እና ማሳወቅ ቡድን መሪ ሌተናል ኮሎኔል አዲሱ ሽፈራው ሁሉም የመከላከያ ክፍሎች በሚባል አግባብ መመዝገብ የሚገባቸው የሠራዊቱ አመራሮች ህግና አሠራርን ተከትለው ሀብታቸውን እያሥመዘገቡ እንደሚገኙ አስረድተዋል፡፡

ምዝገባውም ከቅድመ ወንጀል መከላከል ዘዴዎች አንዱ መሆኑንም አንስተዋል፡፡

በየጊዜው ከፌዴራል ሥነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ጋር በመቀናጀት ሥራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙም ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.