Fana: At a Speed of Life!

በገጠር ለሚገኙ ሴቶች የትምህርት ዕድል እንዲመቻችና የሴቶች ፖለቲካዊ ተሳትፎ እንዲያድግ ድጋፍ ማድረግ ይገባል ተባለ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 13 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን የአፍሪካ ህብረት የሰላምና ፀጥታ ምክር ቤት የሚኒስትሮች ስብሰባን በበይነ መረብ ተሳትፈዋል፡፡
ስብሰባው “ ሴቶች ለሰላም፣ ለባህልና የሴቶች አካታችነት በአፍሪካ “ በሚል ርዕስ በሚኒስትሮች ደረጃ የተዘጋጀ ነው፡፡
አምባሳደር ሬድዋን ኢትዮጵያ ባለፉት ሦስት ዓመታት ውስጥ በፌዴራል እና በክልል ደረጃ ሴቶችን በከፍተኛ የመሪነት ቦታዎች ማሳተፏን እንዲሁም በርካታ ሴቶችን በሰላም ማስከበር ማሰማራቷ፤ የሚያኮራት ተግባር መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
ኮቪድ-19 ምክንያት ሴቶችን ለኢኮኖሚያዊ ጫና፣ ከትምህርት ገበታቸው እንዲርቁ፣ ያለዕድሜ ጋብቻ እንዲመሰርቱ እና ለቤት ውስጥ ጥቃቶች ተጋላጭ እንዲሆኑ እንዳደረጋቸውም አስረድተዋል፡፡
ከዚህ በፊት በሴቶች ዙሪያ የተገኙ አበረታች ውጤቶች ወደ ኋላ እንዳይመለሱ በትኩረት መስራት እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡
ሴቶች ለማህበረሰቡ ከሚያበረክቱት ፋይዳዎች አንጻር በተለይም በገጠር ለሚገኙ ሴቶች የትምህርት ዕድል እንዲመቻች፤ የሴቶች ተሳትፎ በፖለቲካ እንዲያድግ ድጋፎች መደረግ እንዳለበት መጠየቃቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.