Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በሚገኘው ወፍ ዋሻ ደን ላይ የእሳት ቃጠሎ ተነሳ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 13 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በሚገኘው ወፍ ዋሻ ደን ላይ የእሳት ቃጠሎ ተነሳ፡፡

ቃጠሎው ከረፋዱ 5 ሰዓት አካባቢ ነው የተነሳ ሲሆን፥ በአንኮበር ወረዳ በሚገኘው የደኑ ክፍል ላይ መነሳቱ ታውቋል፡፡

እስካሁን 3 ቀበሌዎችን በማካለል፥ በዘጎ፣ መስጫ፣ እመምህረት ቀበሌዎች በሚገኘው የደን ሀብት ላይ ጉዳት አድርሷልም ነው የተባለው፡፡

የእሳት ቃጠሎውን ለማጥፋት የአካባቢው ነዋሪ ጥረት እያደረገ ሲሆን አሁን ላይ እሳቱ ከአቅማቸው በላይ ሆኖ በፍጥነት እየተስፋፋ መሆኑን የአንኮበር ወረዳ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ነጋሽ ተከተል ለለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡

የእሳት አደጋውን ለመቆጣጠርም አስቸኳይ የመንግስት ድጋፍ ያስፈልጋልም ነው ያሉት፡፡

የእሳት ቃጠሎ መነሻው ከግለሰብ ማሳ የተነሳ እሳት ወደጫካው በመግባቱ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

በዘላለም ገበየሁ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.