Fana: At a Speed of Life!

የቲቢ በሽታ ይገኝባቸዋል ተብሎ ከሚታሰቡ 157 ሺህ ሰዎች 29 በመቶ ያህሉ ወደ ህክምና አልመጡም- ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) 15ኛው አመታዊ የቲቢ ምርምር ጉባኤና በዓለም ለ39ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ24ኛ ጊዜ የሚከበረው የዓለም ቲቢ ቀን መድረክ እየተካሄደ ነው፡፡
መድረኩ “የቲቢ በሽታን ለመግታት ጊዜው አሁን ነው! “በሚል መሪ ቃል ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡
የጤና ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ደረጀ ድጉማ እንዳሉት ምንም እንኳ በተሰሩ ስራዎች ከፍተኛ መሻሻል ቢኖርም አሁንም ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ በቲቢ በሽታ እየተጠቁ ካሉ 30 ሀገራት አንዷ በመሆኗ ብዙ ስራዎች ይቀራሉ ፡፡
በዓመት 157 ሺህ ሰዎች በቲቢ እንደሚያዙ የጠቆሙት ዶክተር ደረጀ በሽታው እንደሚገኝባቸው ከሚታሰቡ ሰዎች 29 በመቶ ያህሉ ወደ ህክምና እንዳልመጡ ገልፀዋል፡፡
በተጨማሪም መድኃኒት የተላመደ ቲቢ ስርጭት መጨመሩን በሽታው እንደሚገኝባቸው ከሚታሰቡ ሰዎች መካከል መለየት የተቻለው 41 በመቶ ያህሉን መሆኑን ጠቅሰው በሽታውን ለመከላከል ትኩረት ሊደረግ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የውስጥ ደዌና የሳንባ ስፔሻሊስት ዶክተር አምሳሉ በቀለ በበኩላቸው÷ የቲቢና የኮሮና በሽታ ምልክቶች ተመሳሳይ በመሆናቸው ሳል ያለባቸው ሰዎች ኮሮና እንደያዛቸው በማሰብ በቤታቸው የመቆየት አዝማሚያ ማሳየታቸውን ገልፀው በተለይ ሁለት ሳምንትና ከዛ በላይ የቆየ ሳል ሲኖር መመርመር ያስፈልጋል ማለታቸውን ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.