Fana: At a Speed of Life!

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ እና የአፋር ክልል የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ እና የአፋር ክልል የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡
የመግባቢያ ስምምነቱ በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ይድነቃቸው ወርቁ እና በአፋር ክልል የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ መሐመድ አህመድ ተፈርሟል፡፡
የመግባቢያ ስምምነቱ በዋናነት የበይነ መረብ ደህንነት ተጋላጭነት ላይ የዳሰሳ ጥናት ማድረግና ተጋላጭነቱን መቀነስ የሚያስችሉ የመፍትሄ ሃሳቦችን እና ምርጥ ተሞክሮችን ማጋራት፣ መሰረታዊ የበይነ መረብ ደህንነት ምክረ ሃሰቦችን ማቅረብ፣ የበይነ መረብ ደህንነት ተቋማዊ መዋቅሮችን መንደፍ፣ የበይነ መረብ ደህንነት ፍተሻ እና ምዘና ማካሄድ እንዲሁም በተቋሙ የኤሌክትሮኒክስ ደህንነት ላይ ምክረ ሀሳብን ማቅረብ ያተኮሩ ናቸው ተብሏል፡፡
ከዚህ ባለፈም የክልሉን የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ የፕሮጀክት አስተዳደር ስርዓት እና ኢርፒ (የኢንተር ፕራይዝ ሀብት እቅድ) አውቶሜሽን ሲስተሞችን ማልማት፣ የተቋሙን የሰነድ፣ የካዳስተር እና የመሬት አያያዝ መረጃ ስርአቱን ማዘመን፣ የተቋሙን ዳታ ሴንተር መገንባት፣ የበይነ መረብ ደህንነት ግንዛቤ እና የአቅም ግንባታ ዘርፎችን ማጎልበት ስምምነቱ ላይ የተካተቱ ዋና ዋና የትኩረት ነጥቦች እንደሆኑ በፊርማ ስነ-ሥርአቱ ወቅት መገለፁን ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.