Fana: At a Speed of Life!

የኮቪድ19 ወረርሽኝ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኮቪድ19 ወረርሽኝ አሁንም በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

ባሳለፍነው ሳምንት ከነበረው የቫይረሱ የመያዝ አቅም እና በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እያሻቀበ መሆኑንም ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ተናግረዋል።

በዚህም ባሳለፍነው ሳምንት ብቻ ከ13 ሺህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ በስምንት ቀናት ውስጥ ብቻ ከ118 በላይ ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል ነው ያሉት።

የፅኑ ህሙማን ቁጥርም ባለፈው ሳምንት ከነበረት 460 ወደ አሁን ላይ ከ600 በላይ ማሻቀቡም ተነስቷል።

ይህንን ተከትሎም ለፅኑ ህሙማን አጋዥ መተንፈሻ የኦክስጅን እጥረትን ለመፍታት እየሰራ ቢሆንም ህብረተሰቡ የራሱን የመከላከል ሃላፊነት መውሰድ እንዳለበትም ተነስቷል።

የሚደረጉ ሰብሰባዎችን በተመለከተ ማብራሪያ የሰጡት ሚኒስትሯ ከዚህ በኋላ ሊኖሩ የሚችሉ ስብሰባዎችን ማስቀረት ሳይሆን የኮቪድ19 መከላከል በሚያስችል መልኩ መሆን እንዳለበትም ሚኒስትሯ ተናግረዋል።

በተጨማሪም የመዝናኛ እና የምሽት ቦታዎችን እንዲሁም የንግድ ቦታዎች ላይ የሚኖረውን ኮቪድን የመከላከል ስራ ክትትል እንደሚደረግበትም ተጠቁሟል።

የፀጥታ አካላትም ህብረተሰቡ ተገቢውን ኮቪድ19 ለመከላከል የወጡ መመሪያዎችን እንዲተገብሩ ክትትል እንደሚደረግ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መላኩ ፋንታ ገልጸዋል።

ለዚህም ክትትል የሚያደርግ ግብረ ሃይል ተቋቁሞ እየተሰራ ስለመሆኑ አንስተዋል።

ከፀጥታ አካላት ባለፈ ተቋማትም ኮቪድ19ኝን ለመከላከል የተቀመጡ መመሪያዎችን የማስተግበር ሃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባም አሳስበዋል።

በይስማው አደራው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.