Fana: At a Speed of Life!

6ኛው ሀገር አቀፍ ምርጫን በተመለከተ ጋዜጠኞች ትክክለኛ መረጃ ለህዝቡ ማድረስ በሚችሉበት ሂደት ላይ ስልጠና እየተሰጠ ነው

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) 6ኛው ሀገር አቀፍ ምርጫን በተመለከተ ጋዜጠኞች ትክክለኛ መረጃ ለህዝቡ ማድረስ በሚችሉበት ሂደት ላይ ስልጠና እየተሰጠ ነው፡፡
ስልጠናውን ጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲና የአሜሪካን ኤምባሲ ከኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ጋር በመተባበር የሚሰጥ ሲሆን ጋዜጠኞች ከየትኛውም የፖለቲካ ፓርቲ ተፅዕኖ እና ወገንተኝነት ነፃ በመሆን ትክክለኛውን መረጃ ለህዝቡ እንዲያደርሱ ግንዛቤ የሚፈጥር ነው ተብሏል።
በጆንስ ሆፕኪንስ ማዕከል የኮሙዩኒኬሽን ፕሮግራም ዲዛይንና ትግበራ ዳይሬክተር አቶ ብሩክ መላኩ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት ስልጠናው ጋዜጠኞች የየትኛውም ፖለቲካ ፓርቲ አስፈፃሚ ሳይሆኑ ከምርጫ በፊት፣ በምርጫ ወቅትና ከምርጫ በኋላ ያሉ ኩነቶችን በተመለከተ ትክክለኛ መረጃ ለህዝቡ እንዲያደርሱ ዓላማ ያደረገ ነው፡፡
ከዚህም በተጨማሪ ምርጫው ሰላማዊ፣ ፍትሀዊና ዴሞክራሲያዊ እንዲሆን ያግዛል ነው የተባለው።
በጅማ ከተማ እየተሰጠ ባለው ስልጠና ላይ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የሚገኙ የተለያዩ ሚዲያ ተቋማት ጋዜጠኞች እየተሳተፉ ሲሆን በሀገር አቀፍ ደረጃ በአጠቃላይ 700 ጋዜጠኞች ስልጠናውን እንደሚያገኙ ዳይሬክተሩ ገልጿል።
በሙክታር ጣሃ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.