Fana: At a Speed of Life!

ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የመራጮች መመዝገቢያ ቁሳቁስ ወደ ምርጫ ክልሎች ማሰራጨት ጀመረ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የመራጮች ምዝገባ የሚከናወንባቸውን ቁሳቁስ ወደ ምርጫ ክልሎች ማሰራጨት መጀመሩን ገለፀ።
ቦርዱ ከትናንት ጀምሮ በሁሉም የምርጫ ክልሎች የመራጮች ምዝገባ የሚከናወንባቸውን ቁሳቁስ የያዙ ሠማያዊ ሳጥኖችን ማጓጓዝ ጀምሯል።
በዚሁ መሰረት ለ49 ሺህ 407 የምርጫ ጣቢያዎች ለእያንዳንዳቸው የመራጮች ምዝገባ የሚከናወንባቸውን ቁሳቁስ የያዘ አንድ ሠማያዊ ሳጥን እንዲዳረስ ስርጭቱ ተጀምሯል።
በሠማያዊው ሳጥን ውስጥ ዘጠኝ ዓይነት የመራጮች ምዝገባ ማከናወኛ ቁሳቁስ እንደሚገኙበት የገለጸው ቦርዱ፤ የመራጮች ምዝገባ ካርድ፣ የጽሕፈት መሣሪያ ዕቃዎች፣ በምርጫ ወቅት የሚጠቅሙ ቅፆች፣ መመሪያዎች፣ ፖስተሮችና የኮቪድ-19 መከላከያ ቁሳቁስ እነደሆኑ ተገልጿል።
በአገር አቀፍ ደረጃ ለሚከናወነው 6ኛው አገራዊ ምርጫ የኦሮሚያ፣ የሱማሌና የአፋር ክልሎች የምርጫ ምዝገባ ቁሳቁሶች የተዘጋጁት በየቋንቋቸው ሲሆን የተቀሩት ክልሎች በአማርኛ ተዘጋጅቷል።
የመራጮች ምዝገባ የሚከናወንበት ሠማያዊ ሳጥን በእያንዳንዱ ክልልና የምርጫ ጣቢያ እስኪደርስ ምስጢሩ የተጠበቀና በፀጥታ ኃይሎች እጀባ የሚጓጓዝ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.