Fana: At a Speed of Life!

የሲሚንቶ ምርት ስርጭት እየተሻሻለ መምጣቱን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 14፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በመዲናዋ የሲሚንቶ ምርት ስርጭት እየተሻሻለ መምጣቱን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስታወቀ፡፡

ይህንን ያሉት የቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱልፈታ የሱፍ ናቸው፡፡

ሃላፊውና በክፍለከተማና ወረዳ የሚገኙ የዘርፍ አመራሮች ዛሬ በቦሌ ክፍለ ከተማና በቦሌ ለሚ ክፍለ ከተማ የሲሚንቶ አቅርቦትና ስርጭት ያለበትን ደረጃ ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡

ባረጉት ምልከታም የሲሚንቶ አቅርቦቱም ሆነ ስርጭቱ እየተሻሻለ እንደሚገኝ ለማረጋገጥ መቻሉን ገልጸዋል፡፡

መንግስት አከፋፋዮችንና ቸርቻሪ ነጋዴዎችን በየክፍለ ከተማው በመደልደልና በማስተሣሠር ለተጠቃሚው ህብረተሰብ በቀጥታ እንዲደርስ እየተደረገ እንደሚገኝ ገልጸው ህገወጥ በሆነ መልኩ በሚንቀሳቀሱት የንግድ ተቋማት ላይ ደግሞ የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ኃላፊው መግለጻቸውን ከአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.