Fana: At a Speed of Life!

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ 47 ሺህ 459 የተማሪ ቅበላና ጥቅል የመማር ማስተማር አቅም ላይ መድረሱን ገለፀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የጎንደር ዩኒቨርሲቲ በ2008 ዓ.ም ከነበረው ከ28 ሺህ 375 የተማሪ ቅበላና ጥቅል የመማር ማስተማር አቅም በ2012 ዓ.ም ወደ 47 ሺህ 459 ላይ መድረሱን አስታወቀ።
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ በአስር አመት መሪ የልማት እቅዱ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አድርጓል።
የዩኒቨርስቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር አስራት አጸደ ወይን ከ2007 ዓ.ም እስከ 2012 ዓ.ም ድረስ ከፍተኛ ለውጥ ማስመዝገብ የተቻለባቸውን ተግባራት መከወን ችሏል ብሏል።
ዩኒቨርስቲው በ2008 ዓ.ም የነበረውን የተማሪ ቅበላና ጥቅል የመማር ማስተማር አቅም ከ28 ሺህ 375 በ2012 ዓ.ም ወደ 47 ሺህ 459 ማሳደግ እንደቻለ የተናገሩት ዶክተር አስራትየተመራቂ ተማሪዎችን ቁጥርም በአመት 12 ሺህ 600 ማድረስ ተችሏል ብለዋል።
በአምስት አመቱ የልማት እቅድ የትምህርት ጥራትን ማሻሻል የሚችሉ አሰራሮችን በማዘጋጀትና ለምርምር ስራዎች የሚሆን በጀትን ከፍ በማድረግ ተማሪዎች ውጤታማ መምህራኑም አለም አቀፍ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ መሰራቱን ተናግረዋል።
በማህበረሰብ አገልግሎት ተግባራት የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አስተዋፅኦን እንዳበረከተ የገለፁት ፕሬዚዳንቱ በቀድሞው ሰሜን ጎንደር ዞን እና ጎንደር ከተማ አስተዳደር የሚገኙ የመንግስት ትምህርት ቤቶች የደረጃ መሻሻልና የትምህርት ጥራት እንዲያስመዘግቡ የበኩሉንሚና እንደተጫወተም ተናግረዋል።
በጤናው ዘርፍም የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጁ ከስፔሻላይዝድ ሆስፒታሉ ጋር በመተባበር ዜጎች የተለያዩ የህክምና አገልግሎቶችን እንዲያገኙ ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል።
ኮቪድ 19ን በመከላከሉ ረገድም ቀላል የማይባሉ ተግባራትን እንዳከናወነ ዶክተር አስራት ተናግረዋል።
በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ውስጥ ለሚገኙና ፍትህን ለሚሹ ዜጎችም የነፃ ህግ ድጋፍ አገልግሎት ከመስጠት ጀምሮ ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በመሆን የሰላምና ደህንነት ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝም ገልፀዋል።
ዩኒቨርሲቲው የበጀት አቅሙን ከጊዜ ወደ ጊዜ በማሳደግ ሰፋፊ መሰረተ ልማቶችን እያከናወነ እንደሚገኝ እና በአሁኑ ሰአትም 29 ያህል ትልልቅ ፕሮጀክቶች ወደ ተግባር ገብተዋል ነው ያሉት።
የጎንደር ዩኒቨርስቲ ያከናወናቸውን ተግባራት በመመልከትና በመገምገም አለምአቀፍ ተቋማትና የሀገሪቱ መንግስት በርካታ እውቅናና ሽልማቶችን እንዳበረከቱለትም ጠቁመዋል።
በሙሉጌታ ደሴ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.