Fana: At a Speed of Life!

የቱሉሞዬ እንፋሎት ፕሮጀክት የመጀመሪያው ጉድጓድ ቁፋሮ መጠናቀቁ ተገለጸ ፕሮጀክት የመጀመሪያው ጉድጓድ ቁፋሮ መጠናቀቁ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአርሲ ዞን ኢተያ አካባቢ የተጀመረው የቱሉሞዬ የከርሰ ምድር እንፋሎት ኃይል ማመንጫ ግንባታ የመጀመሪያው ጉድጓድ ቁፋሮ መጠናቀቁ ተገለጸ፡፡

ፕሮጀክቱ 150 ሜጋዋት ኃይል ለማግኘት በሁለት ምዕራፎች እየተከናወነ ነው ተብሏል፡፡

የፕሮጀክቱ የቴክኒክ ኃላፊ ስጉርጉር ጌሪሰን እንደተናገሩት ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ የምትገኝ ሀገር በመሆኗ  የእንፋሎት ኃይል ለማመንጨት የሚያስችል ከፍተኛ እምቅ አቅም አላት ብለዋል፡፡

በቱሉሞዬም እስከ 2000 ሜጋ ዋት ኃይል ማመንጨት የሚያስችል እምቅ የእንፋሎት ኃይል መኖሩንም ነው ኃላፊው የተናገሩት፡፡

በሁለት ምዕራፎች 150 ሜጋዋት ኃይል ለማግኘት 10 የተለያዩ ጉድጓዶች እንደሚቆፈር የገለፁት ኃላፊው ለሥራው የሚያግዙ ሦስት የውሃ ጉድጓዶች ቁፋሮ መጠናቀቁንና አራተኛውም በጅምር ላይ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

የፕሮጀክቱ የሳይት ሥራ አስኪያጅ ሩፋት ማይና በበኩላቸው የመጀመሪያው የኃይል ማመንጫ ጉድጓድ ቁፋሮ ተጠናቆ ወደ ሁለተኛው ቁፋሮ መገባቱን ተናግረዋል፡፡

ወደ መሬት ውስጥ መቆፈር ከሚያስፈልገው 2 ሺህ 500 ሜትር ውስጥ አሁን ላይ 1 ሺህ 14 ሜትር መቆፈሩንም ነው የገለጹት፡፡

በቱሉሞዬ ጂኦተርማል እና በኬንያው ኬንጄን ኩባንያዎች ግንባታው እየተከናወነ የሚገኘው፡፡

ግንባታው በ800 ሚሊየን ዶላር ወጪ የሚከናወን ሲሆን ሁለት ዓመታትን እንደሚወስድ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ያገነነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.