Fana: At a Speed of Life!

አቶ ሽመልስ አብዲሳ በአዳማ ከተማ በ168 ሄክታር መሬት ላይ የለማ የስንዴ ማሳን ጎበኙ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ የተመራ ልዑክ በአዳማ ከተማ በ168 ሄክታር መሬት ላይ የለማን የስንዴ ማሳን ጎበኘ፡፡

የስንዴ ማሳው በመስኖ የለማ መሆኑን የአዳማ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ኃይሉ ጀልዴ ገልጸዋል፡፡

በጉብኝቱ ላይ የገንዘብ ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ኢዮብ ተካልኝ፣ የኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ፍቃዱ ተሰማና የኦሮሚያ ግብርና ተፈጥሮ ሀብት ኃላፊ አቶ ዳባ ደበሌ መገኘታቸውን ኦቢኤን ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.