Fana: At a Speed of Life!

የኬንያ ላሙ ወደብ በመጪው ሰኔ ወር ለኢትዮጵያ አገልግሎት መስጠት ይጀምራል

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኬንያ ላሙ ወደብ በመጪው ሰኔ ወር ለኢትዮጵያ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር ተገለጸ፡፡

የላፕሴት ፕሮጀክት ሊቀመንበር ሜጀር ጀነራል ቲቱሱ ኢቡይ በሰኔ ወር ከኢትዮጵያ ዕቃ ማጓጓዝ እንደሚጀምር አስታውቀዋል፡፡

ሊቀመንበሩ ቀሪ ስራዎችን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑንም አንስተዋል፡፡

የላሙ ወደብ የመርከቦች ማቆያ የላፕሴት ኮሪደር ፕሮጀክት አካል ነው።

ፕሮጀክቱ ኢትዮጵያን፣ ኬንያን እና ደቡብ ሱዳንን እርስ በእርስ ያስተሳስራል ተብሏል፡፡

ታህሳስ ወር ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድና የኬንያው ፕሬዚዳንት አሁሩ ኬንያታ የወደብ ግንባታው ያለበትን ደረጃ መጎብኘታቸው ይታወሳል፡፡

የወደቡ አጠቃላይ  ወጪ ወደ 5 ቢሊየን ዶላር እንደሚገመትም መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.