Fana: At a Speed of Life!

የአውሮፓ ህብረት ከኢትዮጵያ ጋር ላለው ስትራቴጂክ አጋርነት ልዩ ቦታ እንደሚሰጥ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ህብረት ከኢትዮጵያ ጋር ላለው ስትራቴጂክ አጋርነት ልዩ ቦታ እንደሚሰጥ አስታወቀ፡፡

የገንዘብ ሚኒስትሩ አሕመድ ሽዴ ከአውሮፓ ህብረት ኮሚሽነር የዓለም አቀፍ አጋርነት ኮሚሽነር ዩታኧርፕላይነ እና ከህብረቱ ኮሚሽነር የቀውስ አስተዳደር ያኔስ ሌንአሲስ ጋር በብራሰልስ ተወያይተዋል፡፡

በቆይታቸውም ሚኒስትሩ ለኮሚሽነሮቹ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ሚኒስትሩ በመጪው ሃገራዊ ምርጫ ጉዳይና በትግራይ ክልል ስላለው የሰብዓዊ መብት ጉዳይ ዙሪያ የመንግስትን አቋም አስረድተዋል፡፡

በተጨማሪ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ድርድር ያለበትን ሁኔታ በተመለከተ ገለጻ አድርገዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም ኢትዮጵያ ከህብረቱ ጋር በምታካሂደው የልማት ትብብር ላይ መክረዋል፡፡

ኮሚሽነሮቹ በበኩላቸው ህብረቱ ከኢትዮጵያ ጋር ለመሰረተው አጋርነት ልዩ ቦታ እንዳለው ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ ላላት ገንቢ ሚና ህብረቱ ዋጋ እንደሚሰጥ ማስታወቃቸውን  በቤልጂየም የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.