Fana: At a Speed of Life!

በኑሮ ውድነት መንስኤና የመፍትሄ ሀሣቦች ዙሪያ ያተኮረ ሀገር አቀፍ መድረክ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 16 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በኑሮ ውድነት መንስኤና የመፍትሄ ሀሣቦች ዙሪያ ያተኮረ ሀገር አቀፍ መድረክ እያካሄደ ነው።

በውይይቱ ላይ የኑሮ ውድነት መንስኤዎችን የተመለከቱ የመነሻ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት እየተደረገባቸው ነው፡፡

በመድረኩም አሁናዊው የኑሮ ውድነት መነሻ ምንድን ነው? መፍትሄውስ? በሚል የምጣኔ ሃብት ባለሙያው አቶ ሁሴን አሊ የመነሻ ፅሁፍ አቅርበዋል፡፡

በፅሁፋቸውም ከዚህ ቀደም ከልክ ያለፈ ገንዘብ በኢኮኖሚው ውስጥ መሰራጨቱ፣ የምጣኔ ሃብቱ ከአምራች ዘርፍ ይልቅ በአገልግሎት ዘርፉ ላይ መንጠልጠሉ፣ የምርትና ምርታማነት አለመጨመርና በወጪና ገቢ ንግድ መካከል ያለው ልዩነት እየሰፋ መሄዱን እንደ ችግር ጠቅሰዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም የማህበራዊና ፖለቲካዊ ቀውሶች መፈጠር፣ የንግድ እንቅስቃሴዎች ያልተረጋጋ መሆን፣ የንግድ ስርአቱ ገበያ መር ከመሆን ይልቅ በደላላ መመራቱ እና ሌሎች ችግሮችንም ዘርዝረዋል፡፡

በምስክር ስናፍቅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.