Fana: At a Speed of Life!

የፕሬዚዳንት ጆ  ባይደን መልዕክተኛ  ሴናተር ክሪስ ኩንስ በኢትዮጵያ ትልቅ ለውጥ እንደሚኖር አመለከቱ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን መልዕክተኛ ሆነው ኢትዮጵያ መጥተው የነበሩት ሴናተር ክሪስ ኩንስ በኢትዮጵያ ትልቅ ለውጥ እንደሚኖር የሚያመላክቱ ተስፋ ሰጪ ሁኔታዎች መኖራቸውን አመለከቱ።

በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ በተመለከተ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር እንዲወያዩ በፕሬዚዳንት ጆ  ባይደን የተላኩት ሴናተሩ  የጉዟቸውን ውጤት በተመለከተ ትናንት ለሴኔት አቅርበዋል።

ሴናተሩ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድና ሌሎች የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ጋር የነበራቸው ቆይታ መልካም እንደነበር በመግለጽ ምስጋና አቅርበዋል።

ጉዟቸው በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ትልቅ መሻሻል እንዳለ የተመለከቱበት እጅግ ወሳኝ እንደነበር አስረድተዋል።

በኢትዮጵያ ያሉትን ችግሮች ለመፍታት ዝግጁነት እንዳለ በመግለጽ÷ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰሞኑን ባደረጉት ንግግር ያሳዩትን የመንግስት ቁርጠኝነት በአብነት አንስተዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት ከሱዳን ጋር ያለውን የድንበር ውዝግብና የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ጉዳይ በድርድር ለመፍታት ያለውን ዝግጁነት በተመለከትም አድናቆታቸውን ገልጸዋል።

ቀጣይነት ያለው የሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረግ፣ ቀውሱን ለመፍታትና ቀጣዩ አገራዊ ምርጫ ፍትሃዊ እንዲሆን እየተሰራ ያለው ስራ ተስፋ ሰጪ መሆኑን እንደተገነዘቡ ተናግረዋል።

እንቅስቃሴው የሚደነቅና ድጋፍ የሚያስፈልገው መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.