Fana: At a Speed of Life!

የጉሙሩክ ሂደቱን ሳይጠብቁ ሃገር ውስጥ ገብተው ከተሸጡ እቃዎች ከ82 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሞጆ ጉሙሩክ ወደብ የጉሙሩክ ስነ ስርአት ሂደቱን ሳይጠብቁ ከውጭ ሃገር የገቡ 68 ኮንቴነር እቃዎች ተሸጠው 82 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር ታክስና ቀረጣቸው ገቢ ተደረገ።
ሮኒክስ፣ የፋብሪካ ጥሬ እቃዎችና የግንባታ ግብአቶች የሚገኙበት ሲሆን፥ እቃዎቹ በተለያዩ ጊዜያት ወደ ሃገር ገብተው በቀነ ገደባቸው ያልተነሱ ናቸው ተብሏል
የሞጆ ጉሙሩክ ቅርንጫፍ የጉሙሩክ ኦፕሬሽን ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ግርማ በንቲ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት፥ ለእቃዎቹ ባለቤቶች ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶ እቃዎቹን ባለማንሳታቸው ተሸጠው ታክስና ቀረጡ ለመንግስት ገቢ ተደርጓል ብለዋል።
በዚህ መልኩ በአሁኑ ወቅት የጉሙሩክ ስነ ስርአት ሂደቱን ያልጠበቁ 752 ኮንቴነር እቃዎች ከወደቡ የሚነሱበት ቀነ ገደብ በማለፉ በጨረታ ተወግደው ታክስና ቀረጣቸውን ለመንግስት ገቢ ለማድረግ በዝግጅት ላይ መሆናቸውንም ጨምረው ገልፀዋል፡፡
ከእነዚህ ኮንቴነሮች መካከልም 434ቱ ተፈትሸው ለጨረታ ዝግጁ ሆነዋልም ነው ያሉት።
በታሪክ አዱኛ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.