Fana: At a Speed of Life!

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጠ/ሚ ዐቢይ ለተማሩባቸው ትምህርት ቤቶች የ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለተማሩባቸው ሁለት ትምህርት ቤቶች 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የሚያወጡ የትምህርት መርጃ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።

ድጋፍ የተደረገላቸው ትምህርት ቤቶች የበሻሻ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤትና አጋሮ 2ኛ ደረጃ ትምርት ቤት ናቸው።

ዩኒቨርሲቲው 30 ዴስክቶፕ ኮምፒውተር፣ 13 ላፕቶፕ ኮምፒውተር፣ 200 ጠረጴዛና 75 ወንበር እንዲሁም አንድ መኪና ለወረዳው ትምህርት ፅህፈት ቤት ድጋፍ አድርጓል።

ለሴት ተማሪዎች የንፅህና መጠበቂያ ሞዴስ፣ እንዲሁም ሳኒታይዘር፣ ሳሙና እና ደብተር ለትምህርት ቤቶች ድጋፍ ተደርጓል።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሀና ድጋፋ መምህራንና ተማሪዎች ያሉባቸውን ችግሮች በማቃለል ጥራት ያለው ትምህርት ለመስጠት ያግዛል ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በእነዚህ ትምህርት ቤቶች ተምረው ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሳቸውና የሰላም የኖቤል ተሸላሚ መሆናቸው ለበርካቶች መነቃቃትን የፈጠረ በመሆኑ ትምህርት ቤቶች ለድጋፉ መመረጣቸውን ተናግረዋል።

በትምህርት ቤቶች የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለመምህራን የትምህርት እድል እንደሚያመቻችም ፕሬዚዳንቱ ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሀና ቃል ገብተዋል።

የበሻሻ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር አቶ ከድር አርአያ ድጋፉ የትምህርት ቤቱን ችግር እንደሚያቃልል ተናግረዋል።

የጅማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብዱልሀኪም ሙሉ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለትምህርት ቤቶቹ ያደረገው ድጋፍ የተሟላ የመማር ማስተማር ስራ ለማከናወን ትልቅ እገዛ ይኖረዋል ማለታቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.