Fana: At a Speed of Life!

የገቢዎች ሚኒስቴር  ከ 900 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የዓይነት ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)  የገቢዎች ሚኒስቴር በተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ አደጋ የተጎዱ ወገኖችን ለማገዝ የሚውል ከዘጠኝ መቶ ሚሊን ብር በላይ የሚገመት የዓይነት ድጋፍ አደረገ።

ሚኒስቴሩ  “የህዝብን ሀብት ለህዝብ፤ ለወገን ደራሽ ወገን ነው”  መርህን በመከተል የተለያዩ ማህበራዊ ኃላፊነቶችን እየተወጣ እንደሚገኝ ተገልጿል።

በዚህም በዛሬው ዕለት 900 ሚሊየን 503 ሺህ 155 ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የምግብ ምርቶችና የአልባሳት ድጋፍ ለሁሉም ክልሎች፣ ከተማ አስተዳደሮችና ለሜቄዶኒያ የበጎ አድራጎት ማህበር ተሰጥቷል፡፡

በድጋፍ አሰጣጥ ስነስርዓቱ ላይ የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው÷ ተቋሙ ገቢን የመሰብሰብና ኮንትሮባንድን የመከላከል ተልዕኮዎች በአግባቡ እየተወጣ የሚገኝ መሆኑን ጠቁመዋል።

በዚህም ባለፉት ስምንት ወራት 191ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ገቢ መሰብሰቡን ተናግረዋል፡፡

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በአገሪቱ ባጋጠሙ ችግሮች ሁሉ እጁን በመዘርጋት በኮንትሮባንድ የተያዙ እቃዎችን ለጉዳት ለተጋለጡ የህብረተሰብ ክፍሎች በመስጠት የህዝብን ሀብት ለህዝብ እያደረሰ መሆኑንም  ተናግረው÷ባለፉት ስምንት ወራት 1ነጥብ 3 ቢሊየን ብር በአይነት ድጋፍ መደረጉን ገልጸዋል፡፡

የጉምሩክ ኮምሽነር አቶ ደበሌ ቃበታ በበኩላቸው÷ ተቋማቱ ኮንትሮባንድን ከመከላከል ባለፈ ሰብዓዊ ድጋፍ በማድረግ ለጉዳት የተጋለጡ ወገኖችን ሲያግዙ መቆየታቸውን አንስተዋል።

በዛሬው እለት የተሰጠው ድጋፍ በህግ  ማስከበር የተፈጠሩ ችግሮችን፣ የተከሰቱ ግጭቶችን፣ የጎርፍ አደጋዎች፣ የአንበጣ ወረርሽኝን፣ የእሳት ቃጠሎ እንዲሁም የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ታሳቢ በማድረግ የተከፋፈለ መሆኑን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.