Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል የተከሰተውን የዋጋ ንረት ለማስተካከል ክልላዊ ማስፈፀሚያ እቅድ ተዘጋጅቶ እየተሠራ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የተከሰተውን ከፍተኛ የዋጋ ንረት ለማስተካከል ክልላዊ ማስፈፀሚያ እቅድ አዘጋጅቶ ወደ ስራ መግባቱን የአማራ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ገለፀ፡፡
የቢሮው ምክትል ሃላፊ አቶ ተዋቸው እንዳሉት ባለፉት ሁለት ሳምንታት 12 ሺህ 530 የሚደርሱ ድርጅቶች ላይ ፍተሻ ማድረጉን ገልጸው ምርትን ያላግባብ ለብዙ ጊዜ ከዝነው የተገኙና መንግስት ያወጣውን የዋጋ ማስተካከያ ተግባራዊ ያላደረጉ 3 ሺህ 600 የሚደርሱ ድርጅቶች ታሽገዋል ብለዋል፡፡
እንዲሁም እስከ ትናንት ድረስ ገበያ ላይ መዋል ሲገባው ወደፊት የገበያው ዋጋ ይጨምራል በሚል መጋዘን ላይ አላግባብ ተከዝኖ የተገኘ ከ123 ሺህ ኩንታል በላይ ጤፍ፣ በቆሎ፣ ማሽላ እና በርበሬ መገኘቱን አብራርተዋል፡፡
ከዚህ ውስጥ 11 ሺህ 800 ኩንታሉን መንግስት ባወጣው ተመን መሠረት ለህብረተሠቡ ማከፋፈል መቻሉንና ቀሪው በቀጣይ ቀናት የሚከፋፈል መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በዛሬው ዕለት በባህር ዳር ከተማ የሚገኘው የመርከብ ዩኒየን የገበሬዎች ህብረት ስራ ማህበር ስር ተከዝኖ የነበረ 2 ሺህ ኩንታል ጤፍ መንግስት ባወጣው ተመን መሰረት ለሸማቹ ህብረተሰብ ማከፋፈል መቻሉን ከክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.