Fana: At a Speed of Life!

ኢሰመኮ እና በተመድ የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽን ምርመራዎችን በጋራ ለማካሄድ ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽንና /ኢሰመኮ/ በተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽን በትግራይ ክልል አለ ከተባለው ሰብዓዊ መብት ጥሰት ጋር በተያያዘ ምርመራዎችን በጋራ ለማካሄድ ተስማሙ፡፡

ሁለቱ ተቋማት በዛሬው ዕለት በጉዳዩ ዙሪያ የጋራ መግለጫ አውጥተዋል፡፡

ተቋማቱ በሁሉም ወገን ተፈጽመዋል ስለተባሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በጋራ እንደሚመረምሩ ነው ያስታወቁት፡፡

ተቋማቱ ከጥቅምት 24 ጀምሮ በትግራይ ክልል ያለውን የሰብዓዊ መብት አያያዝ ዙሪያ ሲሰሩ እንደነበርም ገልጸዋል፡፡

በመጀመሪያ ዙር ለሦስት ወራት የሚቆዩ ባለሙያዎች በቅርቡ ወደ ስፍራው እንደሚያቀኑ ይፋ አድርገዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.