Fana: At a Speed of Life!

የኤርትራ መንግስት ወታደሮቹን ከኢትዮጵያ ድንበር ለማስወጣት ተስማማ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የኤርትራ መንግስት ወታደሮቹን ከኢትዮጵያ ድንበር ለማስወጣት ተስማማ፡፡

በኤርትራ ጉብኝት እያደረጉ የሚገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ባደረጉት ውይይት ነው ስምምነት ላይ የደረሱት።

በዚህም የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በፍጥነት አካባቢውን እንዲቆጣጠር እና ጥበቃውን እንዲቀጥል ተስማምተዋል፡፡

ሁለቱ ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነታቸው እና የኢኮኖሚ ትስስራቸው ይበልጥ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል።

በፈረንጆቹ 2018 በተደረሰ ስምምነት መሰረት በመተማመን ላይ የተመሰረተ ጉርብትና በጋራ እንገነባለን ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ።

በተለይ በድንበር አካባቢ የሚኖሩ የትግራይ ክልል ዜጎቻችን እና ኤርትራውያን ወገኖቻችንን በመተማመን ላይ የተመሰረተ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ማጠናከር ወሳኝ ነው ሲሉ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.