Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ እና ኤርትራ በድንበር አካባቢ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱን ለማስጀመር ተስማሙ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 17 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና ኤርትራ በድንበር አካባቢ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱን ዳግም ለማስጀመር መስማማታቸውን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ዶክተር አብርሃም በላይ ተናገሩ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኤርትራ ያደረጉትን ይፋዊ ጉብኝት አጠናቀው ተመልሰዋል፡፡

በጉብኝቱ የተሳተፉት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ዶክተር አብርሃም በላይ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት፥ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ተወያይተው ስምምነት ደርሰዋል ።

ህወሓት በሰሜን እዝ ላይ ጥቃት ከሰነዘረ በኋላ ወደ አስመራ ሮኬቶችን በማስወንጨፉ የኤርትራ ሰራዊት ወደ ድንበር እንዲገባ እንዳደረገው ገልጸዋል።

መሪዎቹ በውይይታቸው ህወሓት በሰሜን እዝ ላይ ጥቃት ከሰነዘረ በኋላ ወደ አስመራ ሮኬቶችን በማስወንጨፉ ወደ ድንበር ገብቶ የነበረው የኤርትራ ጦር ከድንበር ሙሉ በሙሉ ለቆ እንዲወጣ እና የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አካባቢውን እንዲቆጣጠር ተስማምተዋል ።

ከዚህ ባለፈም በድንበር አካባቢ በሁለቱ ሀገራት መካከል የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱን ለማስጀመር ስምምነት ላይ ደርሰዋልም ነው ያሉት፡፡

ሁለቱን ሀገራት በልማት ለማስተሳሰር የተጀመሩ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶችን በፍጥነት ለማጠናቀቅ እና አዳዲስ ፕሮጀክቶችን ቀርጾ ለመጀመር መስማማታቸውንም ተናግረዋል፡፡

በዓላዛር ታደለ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.