Fana: At a Speed of Life!

የአይሳኢታ ከተማ መልሶ ግንባታና አቅም ማሳደግ ፕሮጀክት ስራ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፋር ክልል አይሳኢታ ከተማ የሚስተዋለውን የኃይል መቆራረጥና መዋዥቅ ችግር በዘላቂነት ለመፍታት የሚያስችል የማሰራጫ መስመር መልሶ ግንባታ ስራ ተጀምሯል፡፡
የመልሶ ግንባታው ስራው በሁለት ምዕራፍ ተከፍሎ የሚከናወን መሆኑን የአፋር ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት የዲስትሪቢዩሽን ኮንስትራክሽን ኦፕሬሽን ሜይንቴናንስ ሃላፊ አቶ መሃመድ አብዱ ገልፀዋል፡፡
እንደ አቶ መሃመድ ገለጻ የመጀመሪያው ምዕራፍ የመካከለኛ መስመር 13 ነጥብ 8 ኪሎ ሜትር፣ 33 ኪሎ ቮልት እና የ50 ትራንስፎርመር ተከላ እና ማሻሻያ ስራዎችን የያዘ ሲሆን በሁለተኛው ምዕራፍ ደግሞ የ49 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር የዝቅተኛ መስመር ግንባታ ስራ ይከናወናል ተብሏል፡፡
የመልሶ ግንባታና አቅም ማሳደግ ፕሮጀክቱ ዓላማም በከተማው ውስጥ የሚስተዋለውን የኃይል መቆራረጥና መዋዥቅ ችግር በመፍታት የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦቱ ጥራት ያለውና አስተማማኝ እንዲሆን ማድረግ ሲሆን ፕሮጀክቱም በተያዘው በጀት አመት የሚጠናቀቅ መሆኑን ሃላፊው መግለፃቸውን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.