Fana: At a Speed of Life!

የስዊዝ ካናል መዘጋት በየቀኑ 9 ቢሊየን ዶላር ዋጋ ባለው ሸቀጥ ግብይት ላይ መስተጓጎል ፈጥሯል

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የስዊዝ ካናል በአንድ ግዙፍ መርከብ በመዘጋቱ በየቀኑ 9 ቢሊየን ዶላር የሚገመት የሸቀጥ ግብይት ላይ መስተጓጎል እየተፈጠረ መሆኑ ተነግሯል።

ለምስራቁና ምዕራቡ ዓለም ወሳኝ በሆነው በዚህ የውሃ መተላለፊያ መስመር በሰዓት 400 ሚሊየን ዶላር ዋጋ ያለው ግብይት እየተስተጓጎለ ነው ተብሏል።

በዚህ መተላለፊያ በየቀኑ ወደ ምዕራቡ 5 ነጥብ 1 ቢሊየን ዶላር ዋጋ ያለው ሸቀጥ የሚንቀሳቀስ ሲሆን ወደ ምስራቁ ደግሞ 4 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር የሚገመት ሀብት ይዘዋወርበታል ተብሏል።

የውሃ መተላለፊያውን የዘጋችውን መርከብ ለማንቀሳቀስ ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ የሚገኝ ቢሆንም መርከቧን ለማንቀሳቀስ ሳምንታትን ሊወስድ እንደሚችል ቢቢሲ ዘግቧል።

ዘ ኤቨር ጊቭን የተሰኘችው መርከብ የአራት እግር ኳስ መጫወቻ ሜዳዎች ርዝመት እንዳላትና በዓለም ላይ ግዙፍ ከሚባሉ ኮንቴነር ጫኝ መርኮች መካከል አንዷ መሆኗ ይነገራል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.