Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ ለዋልያዎቹ መልካም ውጤት ተመኙ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለኢትዮጵያ የወንዶች ብሄራዊ ቡድን (ዋልያዎቹ) መልካም ውጤት ተመኙ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትዊተር ገፃቸው ላይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ወደ አፍሪካ ዋንጫ የማለፍ ዕድሉን አስፍቷል ሲሉ አስፍረዋል።

ከተለያዩ አካባቢዎች እና ቡድኖች የመጡ ተጨዋቾች በአንድ ዓላማ ተጫውተው ያስገኙት ድል ትልቅ አርአያነት አለው ብለዋል።

በቀጣዩ ጨዋታቸው መልካሙን ሁሉ እመኝላቸዋለሁ በማለት ለቡድኑ መልካም ውጤት ተመኝተዋል።

የኢትዮጵያ የወንዶች ብሄራዊ ቡድን ለአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ የማጣሪያ ጨዋታ እያደረገ ሲሆን ባለፈው ረቡዕ ማዳጋስካርን 4 ለ 0 ማሸነፉ የሚታወስ ነው።

በዚህም በካሜሩን ለሚዘጋጀው የአፍሪካ ዋንጫ የማለፍ እድሉን ያሰፋ ሲሆን ቀጣዩን ጨዋታ ለማድረግ በዛሬው ዕለት ወደ ኮትዲቯር አቅንቷል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.