Fana: At a Speed of Life!

አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ማዕከል እና የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ድርጅት በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ማዕከል እና የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ድርጅት በተለያዩ ዘርፎች በትብብር ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል፡፡
ስምምነቱን የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር
ወርቁ ጋችና እና የኢዜአ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሰይፈ ደርቤ ተፈራርመዋል፡፡
በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ የማዕከሉ ዳይሬክተር ኢንጂነር ወርቁ ጋችና የሰው ሰራሽ አስተውሎት ለሚዲያው ዘርፍ ትልቅ የቴክኖሎጂ መፍትሔን ይዞ የመጣ መሆኑን አመላክተዋል፡፡
ኢዜአ የዚህ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ እንዲሆን የአቅም ግምባታ ስራ እንደሚሰራ መጠቆማቸውን ከማዕከሉ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የኢዜአ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሰይፈ ደርቤ በበኩላቸው ከማዕከሉ ጋር አብሮ መስራት ትልቅ እድል መሆኑን ገልፀው ድርጅቱ በኢትዮጵያ የሚዲያ አገልግሎት ዘርፍ ምሳሌ የመሆን ዓላማን ይዞ ከመነሳቱ አንጻር ግቡን ለማሳካት የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ ትልቅ እገዛ እንደሚኖረው ተናግረዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.