Fana: At a Speed of Life!

ቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማኅበር አሰልጣኝ ፍራንክ ናፓልን ዋና አሰልጣኝ አድርጎ ሾመ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከደቡብ አፍሪካዊው አሰልጣኝ ማሂር ዴቪድስ ጋር በስምምነት የተለያየው ቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማኅበር  አሰልጣኝ ፍራንክ ናፓልን ዋና አሰልጣኝ አድርጎ ሾሟል፡፡

አሰልጣኝ ፍራንክ በእግር ኳሱ ዘርፍ ከ35 ዓመታት በላይ በተለይ በአፍሪካ በማሰልጠን ልምድ ያካበቱና ውጤታማ መሆን የቻሉ መሆናቸውን እግር ኳስ ማህበሩ በፌስቡክ ገፁ አስታውቋል።

በፈረንጆቹ 2015 እና 2016 የኬንያ ፕሪምየር ሊግ ዋንጫ ማንሳታቸው የተገለፀ ሲሆን በተጨማሪ በ2015 የኬንያ ሱፐር ካፕ ምርጥ ስምንት አሸናፊ እንደነበሩ ነው የተነገረው።

እንዲሁም የእንግሊዝ ከ17 አመት በታች ረዳት አሰልጣኝ በመሆን የ2011 አውሮፓ ሻምፒዮን ሆነዋል።

የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ፕሮፌሽናል ላይሰንስ ያላቸው አሰልጣኝ ፍራንክ፣ ካሳኳቸው ድሎች በተጨማሪ ዌስትብሮም፣ ሬንጀርስና ሚድልስቦሮውን ጨምሮ ዛማሌክ፣ ኸርትስ ኦፍ ሆክና ጉርማሂያ ክለቦች በፊትነስ፣ በዋናና ምክትል አሰልጣኝነት አገልግለዋል ።

ከዚህ በተጨማሪ አሰልጣኙ በ2011 የፊፋ ኮቺንግ ኢንስትራክተር በመሆን ያገለገሉ ሲሆን በተጨማሪም የዪ.ኤፋ ኢንስትራክተር በመሆን ሰርተዋል ተብሏል፡፡

አሰልጣኝ ፍራንክ በዛሬው እለት ፊርማቸውን ባኖሩበት ወቅት ቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ የሚፈልገውን ውጤት ለማምጣትም እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.