Fana: At a Speed of Life!

አቶ ሽመልስ አብዲሳ በጅማ ዞን ሰቃ ወረዳ በበጋ መስኖ የለማን የስንዴ ማሳ ጎበኙ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 17 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በጅማ ዞን ሰቃ ወረዳ በበጋ መስኖ የለማን የስንዴ ማሳ ጎበኙ፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በወረዳው በበጋ መስኖ በኩታ ገጠም የለማውን የስንዴ ምርት እየተሰበሰበ ያለበትን ሂደት ተመልክተዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ አርሶ አደሮች ሙሉ የግብርና ፓኬጅ ተጠቅመው በአጭር ጊዜ ውስጥ ውጤታማ መሆን እንደሚችሉ በተግባር አረጋግጠዋል ብለዋል፡፡

በተጨማሪም በኦሮሚያ ክልል በዘንድሮው በጀመሪያው ዙር የበጋ የመስኖ ልማት ከ160 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ስንዴ በኩታ ገጠም መልማቱንና በሁለኛው ዙርም ከ220 ሺህ ሄክታር መሬት በላይ ስንዴ ለማልማት መታቀዱን አቶ ሽመልስ ተናግረዋል።

የጅማ ዞን አስተዳዳሪ አቶ አብዱልሃኪም በበኩላቸው በዞኑ በበጋ መስኖ 30 ሺህ 53 ሄክታር መሬት መልማቱን ጠቅሰው፥ በተገኘው ውጤት በአርሶ አደሩ መነቃቃት ይፈጥራል ብለዋል።

የዘንድሮው የመስኖ ልማት በሃገር አቀፍ ደረጃ በምግብ እህል ራስን ለመቻል የሚደረገውን ጥረት እንደሚያግዝ ተገልጿል።

በሙክታር ጣሃ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.