Fana: At a Speed of Life!

በአሶሳ ከተማ 2 ሚሊየን የሚጠጋ ሃሰተኛ የብር ኖት ከነተጠርጣሪው በቁጥጥር ስር ዋለ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 17 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ 2 ሚሊየን የሚጠጋ ሃሰተኛ የብር ኖት ከነማባዣ ማሽን እና ተጠርጣሪው ጋር ዛሬ በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ፡፡
የፖሊስ መምሪያው ሃላፊ ኮማንደር ቡሽራ አልቀሪብ ፖሊስ የህብረተሰቡን ጥቆማ መሠረት በማድረግ በተጠርጣሪው ቤት ባደረገው ፍተሻ 2 ሚሊየን የሚጠጋ ሃሰተኛ ባለ 200 አዲሱን የብር ኖት ማግኘቱን ገልፀው ከሃሰተኛ ብሮቹ በተጨማሪ በ”ኤፎር ሳይዝ” በህትመት ላይ ያሉ በርካታ ወረቀቶችም መገኘታቸውን ተናግረዋል፡፡
ከሃሰተኛ የብር ኖቱ ባሻገር ተጠርጣሪው ሀሰተኛ የብር ኖት የሚያትምበት ማሽን፣ ኬሚካል፣ ቀለም እና ሌሎችም ቁሳቁሶች በቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉን ገልጸዋል፡፡
እንዲሁም ሃሰተኛ የትምህርት ማስረጃዎች፣ ተጠርጣሪው ድርጊቱን ለመፈጸም ገንዘብ የሚለዋወጥበት ከፍተኛ የብር መጠን የያዙ የተለያዩ የባንክ ሂሳብ ደብተሮችም እንደተገኙ አመልክተዋል፡፡
ከግለሰቡ ጋር ተባባሪ የነበረ አንድ ተጠርጣሪ ለጊዜው መሰወሩን ጠቁመው፤ ፖሊስ ቀሪ የሃሰተኛ ገንዘብ ምንጮችን ለማድረቅ ምርመራ እና ክትትሉን አጠናክሮ መቀጠሉን አስታውቀዋል፡፡
ህብረተሰቡ በግብይት ወቅት ጥንቃቄ እንዲያደርግ ያሳሳቡት ኮማንደሩ፤ ችግሩ በዘላቂነት እንዲወገድ ጥቆማ የመስጠት ድጋፉን እንዲያጠናክር መልዕክት ማስተላለፋቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.