Fana: At a Speed of Life!

የታንዛኒያ የቀድሞው ፕሬዚዳንት የጆን ማጉፉሊ የቀብር ስነ ስርዓት ተፈፀመ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የታንዛኒያው የቀድሞ ፕሬዚዳንት የጆን ማጉፉሊ የቀብር ስነ ስርዓት ተፈፀመ።

የቀብር ስነ ስርዓቱ በታንዛኒያ ሰሜን ምዕራብ በምትገኘው በትውልድ ስፍራቸው ቻቶ ግዛት ተፈፅሟል።

በስነ ስርዓቱ ላይም ቤተሰቦቻቸው እና በሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ሳሚያ ሱሉሁ የሚመራ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ተሳትፈዋል።

ባለፈው ሳምንት በተለያዩ የታንዛኒያ አካባቢዎች ለቀድሞው ፕሬዚዳንት ሽኝት ሲካሄድ ቆይቷል።

ጆን ማጉፉሊ ከልብ ህመም ጋር በተያያዘ ህይወታቸው ማለፉን የሀገሪቱ መንግስት ማስታወቁ የሚታወስ ነው።

ህልፈታቸው ይፋ ከመሆኑ በፊት ለሳምንታት ያህል ከህዝብ ዕይታ ርቀው ነበር።

እስካሁን በመንግስት ወገን ባይረጋገጥም የሀገሪቱ ተቃዋሚዎች ከሁለት ሳምንታት በፊት ፕሬዚዳንቱ ኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው ሲናገሩ እንደነበር ይታወሳል፡፡

ህልፈታቸውን ተከትሎ ምክትል ፕሬዚዳንት የነበሩት ሳሚያ ሱሉሁ ስልጣኑን ተረክቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.