Fana: At a Speed of Life!

ለመንግስት ሠራተኞች ከቀጣዩ ወር ጀምሮ የብቃት ማረጋገጫ ምዘና ሊሰጥ ነው

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 18 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከቀጣዩ ሚያዝያ ወር ጀምሮ ለመንግስት ሠራተኞች የብቃት ማረጋገጫ ምዘና እንደሚሰጥ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አስታወቀ።

በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የሚዘጋጀው ምዘና ብቁና ተወዳዳሪ ሠራተኛ ለማፍራት ወሳኝ ሚና ይኖረዋል ተብሏል።

የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽነር በዛብህ ገብረየስ ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ ወደ መንግስት ተቋማት የሚገቡ ሠራተኞችን ሙያዊ ብቃት ለማረጋገጥ የተለያዩ ተግባራት ሲከናወኑ መቆየታቸውን አስታውሰዋል።

ምዘናው ለሁሉም የመንግስት ተቋማት እንዲያገለግል የጋራ መስፈርት ወጥቶለት መዘጋጀቱንም ገልፀዋል።

ወደ መንግስት ተቋማት አዲስ ለሚገቡትም ሆነ ለነባር ሠራተኞች የብቃት ምዘናውን ለመስጠት በቂ ዝግጅት እስከሚደረግ ከታሰበው በላይ ጊዜ መውሰዱንም ጠቅሰዋል።

በአንዳንድ ተቋማት ሲሰጥ የቆየው የብቃት ምዘና በአዲሱ የምዘና መስፈርት የሚካተት እንደሚሆንና ምዘናውን በግል መስጠት የሚፈልጉ ተቋማትም ከኮሚሽኑ ጋር መዋዋል እንደሚችሉ ጠቁመዋል።

እንደ ኮሚሽነር በዛብህ ገለጻ በቀጣዮቹ ዓመታት የመንግስት ተቋማት የአሰራርና የአደረጃጀት ክፍተቶች በጥልቀት ይፈተሻሉ።

ተመሳሳይ ስራና ዓላማ ይዘው የሚሰሩ ተቋማት ወደ አንድ የሚመጡበት ሁኔታም ይኖራል ብለዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.