Fana: At a Speed of Life!

በድሬዳዋ “የሴቶች አመራር ሚና እና የኢትዮጵያ ብልፅግና” በሚል መሪ ቃል ውይይት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 18 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) “የሴቶች አመራር ሚና እና የኢትዮጵያ ብልፅግና” በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ የውይይት መድረክ በድሬዳዋ እየተካሄደ ነው።

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ባዘጋጁት መድረክ ላይ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብት ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የአጠቃላይ ትምህርት ንዑስ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ ራቢያ ኢሳን ጨምሮ የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ዑባህ አደም ተሳታፊ ሆነዋል።

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብት ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የአጠቃላይ ትምህርት ንዑስ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ ራቢያ ኢሳ ሴቶች ድርብርብ ሀላፊነት እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡

ሴቶች ጠንክረው በመስራት የተጣለባቸውን ሀገራዊ ሀላፊነት በመወጣት ለሌሎችም አርአያ መሆን እንደሚጠበቅባቸው ጠቁመዋል።

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ዑባህ አደም በበኩላቸው ሴቶች ኢትዮጵያ ካላት የህዝብ ብዛት ግማሽ ያህሉን ቢሸፍኑም ያላቸው ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት በጣም ዝቅተኛ መሆኑን አንስተዋል፡፡

ሃገሪቱ የሚያስፈልጋትን ብቁና ተወዳዳሪ የሰው ሀይል ለማፍራት የሴቶች ሚና የማይተካ እንደሆነ በመገንዘብ መስራት ይገባልም ነው ያሉት።

በመድረኩ ላይ የሴት ተማሪዎችን ስኬት ለማሳደግ የሴት የአካዳሚክ አመራሮች ሚና በሚል መነሻ ሀሳብ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

በእዮናዳብ አንዱዓለም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.