Fana: At a Speed of Life!

ከ55 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነቡ የጥልቅ ጉድጓድ የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች ተመረቁ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 18 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)  የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ከ55 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ ያስገነባቸውን አራት የጥልቅ ጉድጓድ የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶችን በዛሬው ዕለት  ተመርቀዋል።

በኮልፌ ቀራንዮና በጉለሌ ክፍለ ከተሞች የተገነቡት የውሃ ፕሮጀክቶቹ እያንዳንዳቸው በቀን 9 ሺህ ሜትር ኪዩብ ውሃ መስጠት የሚችሉ መሆናቸው በምረቃው ወቅት ተገልጿል።

የባለስልጣኑ የአዲስ ክፍለ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር መሰለ ዘውዴ÷የጥልቅ ጉድጓድ ውሃ ፕሮጀክቶቹ በተዘረጉ መስመሮች ለተጠቃሚው እንዲደርሱ  ተደርገው የተገነቡ መሆናቸውን ገልፀዋል።

ፕሮጀክቶቹ በተጠቀሱት አካባቢዎች በሁለት ሳምንት ለአንድ ቀን ብቻ በፈረቃ ይሰራጭ የነበረውን የውሃ አቅርቦት በሳምንት ወደ 2 ቀናት እንዲያድግ ያስችላሉም ነው የተባለው።

የአካባቢው ነዋሪዎችም በፕሮጀክቶቹ ግንባታ መደሰታቸውንና ቀደም ሲል የነበረውን ችግር በከፊል እንደሚያቃልሉ ገልፀዋል።

በቀጣይም መሰል ፕሮጀክቶች ተጠናክረው እንዲቀጥሉና ዘላቂ የውሃ ተጠቃሚነታቸው እንዲረጋገጥ መጠየቃቸውን ኢብኮ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.