Fana: At a Speed of Life!

በጎንደር ከተማ በህገወጥ መንገድ ተከማችተው የተገኙ የግብርና ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ እየከተፋፈሉ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 18 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በጎንደር ከተማ በህገወጥ መንገድ ተከማችተው የተገኙ የግብርና ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ እየከተፋፈሉ መሆኑን የከተማዋ ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ገለፀ።

የከተማው ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ በአራዳ፣ ማራኪና አዘዞ-ፀዳ ክፍለ-ከተሞች ብቻ 35 ሺህ የግብርና ምርቶች በህገወጥ መንገድ ተከማችተው ማግኘቱን አስታውቋል።

በዚህም መምሪያው የንግድ ድርጅቶች ላይ እርምጃ እየወሰደ  እንደሚገኝ ተገልጿል።

የመምሪያው ሀላፊ አቶ አደራጀው አላበ ለጣቢያችን እንዳስታወቁት÷ ምርቶች በሸማች  ማህበራት በኩል ለማህበረሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲሸጡ ተደርጓል።

የቁጥጥርና ክትትል ስራውን በማጠናከር በህገወጥ መንገድ ምርት የሚያከማቹና ያለ አግባብ ዋጋ በሚጨምሩ ድርጅቶች ላይ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን ሀላፊው ተናግረዋል።

በዛሬው ዕለትም በህገወጥ መንገድ የተከማቸ  1 ሺህ 200 ኩንታል  በድብቅ ምርቱን ሊያሸሽ የነበረና 185 ኩንታል እንደጫነ በከተማ አስተዳዳሩ ንግድ መምሪያ ተደርሶበታል ነው ያሉት።

ሀላፊው አያይዘውም ህብረተሰቡ ህገወጥ ነጋዴዎችን በመጠቆም እንዲተባበር  ጥሪ አቅርበዋል።

በኤልያስ አንሙት

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.