Fana: At a Speed of Life!

በሴቶች ላይ የሚደርሰው ጥቃት በአንድ ሰሞን መግለጫ የሚቆም አይደለም-ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 18 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሴቶች ላይ የሚደርሰው ጥቃት በአንድ ሰሞን መግለጫ የሚቆም አይደለም ሲሉ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ተናገሩ።
ፕሬዚደንቷ ይህን ያሉት የሴቶች አመራር ሚና እና የኢትዮጵያ ብልፅግና በሚል ርዕሥ በድሬዳዋ በተዘጋጀው የምክክር መድረክ ላይ ነው።
ሴት አመራሮችን ለማብቃት በሚደረገው ጥረት ውስጥም እርሳቸው የሚጠበቅባቸውን ለመወጣትም ቃል ገብተዋል።
በዚህ ሂደት ላይ የድሬደዋ ዩኒቨርስቲ ከሌሎች አንጋፋ ተቋማት በመቅደም ሴት ፕሬዝዳንትን ወደ አመራርነት ማምጣቱ ሊያስመሰግነው ይገባዋልም ብለዋል።
በመድረኩ ተሳታፊ የሆኑት ሴት መምህራን በበኩላቸው÷ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ የህፃናት ማቆያ(ዴይ ኬር) መከፈት ብቁ የሴት አመራሮችን ለማፍራት በሚደረገው ጥረት ከፍተኛ በመሆኑ ተፈፃሚ እንዲሆንላቸዉ ጠይቀዋል።
በመድረኩ ላይ ፕሬዚዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴን ጨምሮ የሴቶች፣ ህጻናትና ወጣቶች ሚንስትር ወይዘሮ ፊልሰን አብዱላሂ እና የአስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ አቶ ከድር ጀዋር ተገኝተዋል።
በእዮናዳብ አንዱዓለም
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-

https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.