Fana: At a Speed of Life!

አራት ሚሊየን ብር የሚያወጡ የፍጥነት መቆጣጠሪያ መሳሪያዎች ለደቡብ ክልል ተበረከተ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 18 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)የትራንስፖርት ሚኒስቴር አራት ሚሊየን ብር የሚያወጡ በቴክኖሎጂ ፍጥነትን ለመቆጣጠር የሚረዱ አምስት የፍጥነት መቆጣጠሪያ መሳሪያዎችን ለደቡብ ክልል አበርክቷል።
የፍጥነት መቆጣጠሪያው የተበረከተው በክልሉ ከተፈቀደው የፍጥነት ወሰን በላይ በማሽከርከር አደጋ ለሚደርስባቸውና ፍሰት ለሚበዛባቸው አምስት ዞኖች(ለጌዲዮ ፣ጋሞ፣ ወላይታ፣ ጉራጌና ካፋ ) መሆኑም ተመላክቷል።
ይህ የፍጥነት መቆጣጠሪያ እያንዳንዱ ከ ስምንት መቶ ሺህ ብር በላይ እንደሚያወጣም ተገልጿል።
በክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮና ከክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን እንዲሁም ከፌደራል ትራንስፖርት ሚኒስቴር ጋር በመሆን የራዳር አጠቃቀም የንድፈ ሀሳብና የተግባር ስልጠና ለዞኖች የመንገድ ትራፊክ ደህንነት አስተባባሪዎች:የመንገድ ትራፊክ ደህንነት የቁጥጥር ባለሙያዎች ለትራፊክ ባለሙያዎችና ለሌሎች ባለድርሻ አካላት በወላይታ ሶዶ እየተሰጠ ይገኛል።
አቶ ክፍሌ ዋና የደቡብ ክልል ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊና የትራንስፖርት ዘርፍ ሀላፊ÷ ከመንገድ ደህንነት ከመንገድ ዲዛይን እንዲሁም ህግ የማስከበር ስራዎች እንደክልል ትኩረት የተሰጡባቸው ጉዳዮች መሆናቸውን ጠቁመዋል።
በዚህም ከትራንስፖርት ሚኒስቴር ጋር በመቀናጀት አምስት ራዳሮች ለ አምስት ዞኖች መሰጠታቸውን ተናግረዋል።
የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የትራፊክ አደጋ መከላከልና ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮማንደር ታደለ ዋሪዮ ÷ በክልሉ በአሁን ሰአት ያለው የአደጋ ሁኔታ ከአምናው ጋር ሲነፃፀር ቢቀንስም የሞት መጠኑ ግን መጨመሩን ተናግረዋል።
አቶ መርከቡ ታደሰ በክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ የመንገድ ትራፊክ ደህንነትና ኢንፎርሜሽን ብቃት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በበኩላቸው÷ በሰው ሕይወትና ንብረት ላይ የሚከሰተውን የትራፊክ አደጋ ለመከላከል ሁሉም በሀላፊነት ሊንቀሳቀስ ይገባል ብለዋል።
ፍጥነትን ለመቆጣጠር የሚረዳውን ራዳር በጥንቃቄ በመያዝ ዘወትር ሊሰራባቸው ይገባልም ነው ያሉት ።
በእየሩሳሌም ደምሴ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-

https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.