Fana: At a Speed of Life!

መታሰቢያነታቸው ለአገር መከላከያ ሠራዊትና ለተጎጂ ንጹሃን ዜጎች የሆኑ የሙዚቃ ‘ክሊፖች’ ተመረቁ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 18 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአንጋፋው አርቲስት ጌታቸው ጋዲሳ የተዘጋጁት ‘የቁርጥ ቀን ልጅ ነኝ’ እና ‘የንጹሃን ደም’ የተሰኙ መታሰቢያነታቸው ለአገር መከላከያ ሠራዊትና ለተጎጂ ንጹሃን ዜጎች የሁኑ የሙዚቃ ክሊፖች ዛሬ ተመርቀዋል።

በብሔራዊ ቲያትር በተካሄደው የምረቃ ሥነ-ሥርዓት የአርቲስቱ ወዳጆችና የጥበብ አፍቃሪዎች ታድመዋል።

አርቲስት ጌታቸው ጋዲሳ ከአራት አስርት ዓመታት በፊት በሌላ አርቲስት ተዘጋጅቶ የነበረውን ‘የቁርጥ ቀን ልጅ ነኝ’ የተሰኘን ሙዚቃ ዘመኑን እንዲመስል አድርጎ ማዘጋጀቱን ገልጿል።

ከጥንት እስከ ዛሬ ለአገር አንድነትና ህልውና መስዋዕት እየሆነ ያለው የአገር መከላከያ ሠራዊት ተጋድሎ ሊመሰከርለት ይገባል ብሏል።

ሠራዊቱ ዘንድሮም ቢሆን የአባቶቹን ገድል እየደገመ በመሆኑ ይህ በአግባቡ መንጸባረቅ አለበት ነው ያለው።

አርቲስት ጌታቸው ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ንጹሃን ዜጎች በማይመለከታቸው ጉዳይ ሕይወታቸውን እያጡ መሆኑንም አንስቷል።

ለዚህም እንደ ጥበብ ባለሙያነቱ መታሰቢያነቱ ለንጹሃን ዜጎች እንዲሆን ‘የንጹሃን ደም’ የተሰኘ የሙዚቃ ክሊፕ ማዘጋጀቱን ገልጿል።

አርቲስቱ ለሠራዊቱ ክብር ሲባል የተዘጋጀው የሙዚቃ ክሊፕ ባማረ መልኩ ፍጻሜ እንዲያገኝ የመከላከያ ሠራዊት ላደረገለት ድጋፍ ምስጋና አቅርቧል።

በሥነ ሥርዓቱ ላይ በክብር እንግድነት የታደሙት በመከላከያ ሚኒስቴር የጦር ሜዳ ዘጋቢና ወታደራዊ ታሪክ ጸሐፊ ሻለቃ ገበየሁ ዋለልኝ ‘ጥበብ በሠራዊቱ ዘንድ ትልቅ ስፍራ አላት’ ብለዋል።

እንደ እርሳቸው ገለጻ ሠራዊቱ ከአጥንት ከአፄዎቹ ዘመናት ጀምሮ በወኔ ቀስቃሽ የጥበብ ስራዎች ታጅቦ ነው ከጠላት ጋር የሚፋለመው።

የምስራቁን ጦርነት ለአብነት የጠቀሱት ሻለቃ ገበየሁ÷ በሠራዊቱ ኦርኬስትራ ቡድኖች ወኔ ቀስቃሽነት የካራማራ ድል ተገኝቷል ነው ያሉት።

አሁንም አርቲስት ጌታቸው የሠራዊቱን ወኔና ሞራል ከመገንባት ባሻገር አርቲስቱ ለሠራዊቱ ያለውን ክብር የሚያሳይ ነው ብለዋል።

በመርሃ ግብሩ የታደሙ የጥበብ ቤተሰቦች አርቲስት ጌታቸው ሁለገብ ሙያተኛና አገር ወዳድ መሆኑን መስክረውለታል።

ከጥበብ ስራው በተጨማሪ በልማት ስራዎችም እንደሚሳተፍመናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በሥነ ሥርዓቱ ለአርቲስት ጌታቸው ጋዲሳ የእውቅና ሽልማት የተበረከተ ሲሆን÷ አርቲስቱም በሙዚቃዎቹ  ታዳሚዎችን አስደስቷል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.