Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በጂማ ዞን ቀርሳ ወረዳ የተለያዩ የልማት ስራዎች ጎበኙ  

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 18 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ  ሽመልስ አብዲሳ በጂማ ዞን ቀርሳ ወረዳ የተለያዩ የልማት ስራዎች ጎብኝተዋል።

የዛሬው የርዕሰ መስተዳድሩ  ጉብኝት በዘንድሮ ዓመት ሊተከል እየተዘጋጀ ያለው የአቮካዶ እና የቡና ችግኝ ላይ ትኩረቱን ያደረገ ነበር።

ርዕሰ መስተዳድሩ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት ÷በደቡብ ኦሮሚያ አካባቢዎች የሚስተዋለውን የመሬት አሲዳማነት ለመከላከል እንዲሁም አርሶ አደሩን ተጠቃሚ ለማድረግ እና የደን ለሽፋኑንም ከፍ ለማድረግ ታስቦ መንግስት በፍራፍሬ እና የተሻለ ምርት ሊሰጡ የሚችሉ የቡና ዝርያዎች ላይ ትኩረት በማድረግ እየሠራ ነው ብለዋል።

በዛሬው ጉብኝታቸውም ደስተኛ መሆናቸውን በመግለፅ ግብርናን ለማዘመን እየተደረገ ባለው ርብርብ የጂማ ግብርና ምርምር ማዕከል እያደረገ ላለው አስተዋጽኦ አመስግነዋል።

በቀጣይነት የአቮካዶ ምርቱን ከፍ በማድረግ እና እሴት በመጨመር ዘይትን ጨምሮ ሌሎች ምርቶችን ለማምረት መታቀዱንም አንስተዋል።

በጂማ ዞን በ51 የመንግስት ችግኝ ማፍያ 500 ሺህ  ሃስ የተሰኘ የአቮካዶ ዝርያ ችግኝ በእንክብካቤ ላይ መሆኑን እና 297 ሚሊየን ምርጥ ዘር ቡና እየተዘጋጀ መሆኑን የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ አብዱልሃኪም ሙሉ  ተናግረዋል ።

በኦሮሚያ ክልል በዘንድሮ አመት የሚተከል 1ነጥብ 1 ቢሊየን የቡና እና 1ነጥብ 8 ሚሊየን የአቮካዶ ችግኝ በእንክብካቤ ላይ ይገኛልም ተብሏል።

አፈወርቅ አለሙ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.