Fana: At a Speed of Life!

“ከኢትዮጵያ ወደ እየሩሳሌም” በሚል ርዕስ የበይነ መረብ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 18 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በእስራኤል የኢትዮጵያ ኤምባሲ በኢየሩሳሌም ከተማ ከሚገኘው የፖሊሲ ጥናት ተቋም ጋር በመተባበር “ከኢትዮጵያ ወደ እየሩሳሌም” በሚል ርዕስ የበይነ መረብ ውይይት ተካሂዷል።

በበነየ መረብ ውይይቱ ከሦስት መቶ በላይ እስራኤላዊ ምሁራን፣ የሚዲያ ባለሙያዎች እና ተጽእኖ ፈጣሪ ግለሰቦች  የተሳተፉበትን  መሆኑ ተመላክቷል።

ዐውደ ጥናት ትኩረት ከተሰጣቸው ጉዳዮች በቅዱሳን መካናት ከሚገኙት አንዱ ደብረ ሥልጣን መድኃኔዓለም ገዳም ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ፣ በ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በኢትዮጵያዊያን የተገነቡት ሕንጻዎችና የኪዳነ ምህረት ቤተክርስቲያን ናቸው።

አገራችን በኢየሩሳሌም ከተማ ውስጥ ጥንታዊ ሕንጻዎችና ይዞታዎች ያሏት ሲሆን፣ እነዚህ ይዞታዎች ያሉበት አካባቢ አቢሲኒያ መንደር በመባል ይታወቃል።

በእየሩሳሌም ያሉንን ይዞታዎች እንዲጠገኑና፣ በተገቢው መንገድ ጥቅም ላይ እንዲውሉ የዚህ አይነት መድረኮች ትልቅ ፋይዳ  እንዳላቸው ተገልጿል።

በዚህ ውይይት መድረክ በኢትዮጵያ ጉዳይ በርካታ መጽሀፍትን የጻፉት የቴል አቪቭ ዩኒቨርሲቲው ፕሮፌሰር ሀጋይ ኤርሊኽ ፣ ፕሮፌስር ሪሃብ ሪቭሊን፣ ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ዶክተር ጥጋብ በዜ ፣ ከሂብሪው ዩኒቨርሲቲ ዶክተር ቢኒ ፈርስት እንደዚሁም የሥነ ሕንጻ ባለሞያዋ ሻሮን ሽሎስበርግ ጥናታዊ ጽሁፋቸውን አቅርበዋል።

የዚህ አይነት ጉባኤዎች የሁለትዮሽ ግንኙቱን በተለይም የሕዝብ ለሕዝብ ትብብሩን ለማጠናከር ከፍተኛ ፋይዳ እንደሚኖረው ተሳታፊዎቹ ማስታወቃቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.