Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ የሆሚቾ አሙኒሽን ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪን ጎበኙ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 19 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የሆሚቾ አሙኒሽን ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪን ጎበኙ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው የሀገር መከላከያ ሠራዊት የማምረት ዐቅሙን አጠናክሮ በዘላቂነት የሀገርን ሉዐላዊነትን ማስጠበቅ በሚያስችል ቁመና ላይ እንዲገኝ ለውጥ መጀመሩን አስታውሰዋል፡፡
የተጀመረው ለውጥም ትልቅ መሠረት እየጣለ መሆኑንን ዛሬ ሆሚቾ የአሙኒሽን ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪን በመጎብኘት አይተናል ነው ያሉት::
እንዲሁም መከላከያ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ምርቶችን በማምረት በዚህም የራሱን ቁመና አጠናክሮ ወትሮ ዝግጁነቱን በማሳደግ፣ በምርምር የሚልቅበት መሠረታዊ ለውጥ መጀመሩን እንደተመለከቱም ገልፀዋል፡፡
ይሄን አጠናክረን በመቀጠልም የመከላከያ ሁለንተናዊ የተቋም ቁመና እንዲኖረው ቀጣይ ስራዎች እንደሚሰሩም ተናግረዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.