Fana: At a Speed of Life!

የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባዔውን ማካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 19 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)የጋምቤላ ሕዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት 5ኛ የምርጫ ጊዜ 6ኛ የሥራ ዘመን 11ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው ፡፡
ጉባኤው ለ3 ቀናት በሚኖረው ቆይታ የተጠቃለለ የአስፈጻሚ አካላት የ2013 በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት እንደሚደረግበት ይጠበቃል።
በተጨማሪም ጉባኤው የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ የክልሉ ዋና ኦዲት መሥሪያ ቤት፣ የክልል መስተዳድር ምክር ቤት እንዲሁም የክልል ምክር ቤት የ2013 በጀት ዓመት የ6 ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርቶች ለውይይት ቀርበው ይፀድቃሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገልጿል፡፡
እንዲሁም መደበኛ ጉባኤው የተሻሻለው የክልሉ ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ፣ የአካባቢ ተጽዕኖ ግምገማ ፣ የክልሉ አመራር አካዳሚ ፣ የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም እንዲሁም የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ሥልጣንና ተግባር ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ የጉባኤ አባላት መርምረው ውሳኔ እንደሚሰጡበት ይጠበቃል ነው የተባለው፡
ከዚህ ባለፈም ልዩ ልዩ ሹመቶችና ውሳኔዎች ቀርበው እንደሚያፀድቁ ከክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.