Fana: At a Speed of Life!

ከከተማ እስከ ወረዳ የሚገኙ የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች የመስቀል አደባባይ ፕሮጀክትን  ጎበኙ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 19 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ከከተማ እስከ ወረዳ የሚገኙ የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች የመስቀል አደባባይ ፕሮጀክትን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ፣ የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ መለሠ አለሙ እና የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

የመስቀል አደባባይ ፕሮጀክት የለውጡ ትሩፋት  ፕሮጀክት ነው ያሉት ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ፕሮጀክቱ ለሀይማኖታዊ እና ማህበራዊ እንቅስቃሴ ምቹ ከማድረግ ባለፈ ለወጣቶች ሰፊ የስራ እድል እንደሚፈጥር ገልጸዋል ።

ፕሮጀክቱን  ለማጠናቀቅ ቀን ከሌሊት በመሰራት ላይ መሆኑን በመግለፅ በቅርቡ  ፕሮጀክቱን በማጠናቀቅ ለአገልግሎት ክፍት ለማድረግ ይሰራል ማለታቸውን ከከተማዋ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የመስቀል አደባባይ ፕሮጀክት ከወለል በታች 1 ሺህ 4ዐዐ በላይ መኪኖችን ለፓርኪንግ አገልግሎት እንዲሆን ተደርጎ የተገነባ ሲሆን ሱቆችን ጨምሮ ሌሎች አገልግሎት መስጫ  ስፍራዎች ተካተውበታል ።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.