Fana: At a Speed of Life!

ከ5 ቢሊየን ብር በላይ ወጭ የተደረገበት “ደብሊውኤ የዘይት ፋብሪካ” የሙከራ ምርት ጀመረ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 19 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በደብረማርቆስ ከተማ ከ5 ቢሊየን ብር በላይ ወጭ የተደረገበት እና በባለሃብቱ አቶ ወርቁ አይተነው የተገነባው “ደብሊውኤ የዘይት ፋብሪካ” የሙከራ ምርቱን ዛሬ ጀምሯል።

የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገርና ሌሎች የክልልና የዞን ከፍተኛ የሥራ ሀላፊዎችም ፋብሪካው የሙከራ ምርት ሲጀምር  ቦታው መገኘታቸውን አብመድ ዘግቧል።

ፋብሪካው አሁን ላይ ከ1 ሺህ 500 በላይ ለሚሆኑ ወጣቶች የሥራ እድል የፈጠረ ሲሆን በሙሉ አቅሙ ሥራ ሲጀምር ለ3 ሺህ ወጣቶች የሥራ እድል እንደሚፈጥር ታውቋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.