Fana: At a Speed of Life!

በፌደራሊዝም ፅንሰ ሀሳብ ዙሪያ ያተኮረ ስልጠና በጅግጅጋ ተሰጠ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 20 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሰላም ሚኒስቴር በፌደራሊዝም ፅንሰ ሀሳብ ዙሪያ ለሶማሌ ክልል አመራሮች በጅግጅጋ ከተማ ስልጠና ሰጠ።
ሚኒስቴሩ ከመጋቢት 18 እስከ መጋቢት 20 2013 ዓ.ም በሶማሌ ክልል በየደረጃው ለሚገኙ አመራሮች ያዘጋጀው የአሰልጣኞች ስልጠና መስጠቱም ተመላክቷል።
በስልጠናው በክልሉ ከሚገኙ 11 ዞኖች ፣ 93 ወረዳዎችና 6 የከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ አመራሮች ተሳታፊ መሆናቸው ተገልጿል።
ስልጠናውን የሰጡት የሰላም ሚኒስቴር የፌደራሊዝምና የመንግስታት ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ፀጋብርሀን ታደሰ ÷በኢትዮጵያ በየአካባቢው በፌደራሊዝም ፅንሰ ሀሳብ ላይ የሚስተዋሉ የተለያዩ ብዥታዎች መኖራቸውን ጠቁመዋል።
ስልጠናው እነዚህን የአመለካከትና የግንዛቤ ክፍተቶችን ለማሻሻል የተዘጋጀ መሆኑንም ነው ያነሱት።
የስልጠናው ተሳታፊዎች በቀጣይ ወደ የመጡበት አካባቢ ሲመለሱ በተዘጋጁት የስልጠና ማኑዋሎች በመታገዝ ማህበረሰቡን የማሰልጠንና የማወያየት ስራዎችን እንደሚያከናውኑ ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-

https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.