Fana: At a Speed of Life!

የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ዛሬ ወይም ነገ ይፋ ይሆናል

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 20 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ዛሬ ወይም ነገ ይፋ እንደሚሆን የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ አስታወቁ፡፡
ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው የ12ኛ ክፍል ፈተና ዕርማት መጠናቀቁን ጠቅሰው ተፈታኞች ውጤታቸውን ዛሬ ወይም ነገ በ8181 እንዲጠባበቁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ፈተናው በሰላም መጠናቀቁና ኢንተርኔት አለመቋረጡ የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ፈተና ስኬት መሆኑን ያነሱት ሚኒስትሩ በሁለት ሳምንት ዕርማቱ መጠናቀቁ ደግሞ ተጨማሪ ስኬት ነው ብለዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.