Fana: At a Speed of Life!

አምስተኛ ምዕራፍ የልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2 ነጥብ 38 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር የሚተገበረው አምስተኛ ምዕራፍ የልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም ይፋ ሆነ።

በሃገር አቀፍ ደረጃ ከ408 በላይ በሆኑ ወረዳዎች ከ8 ሚሊየን በላይ ዜጎች በልማታዊ ሴፍቲኔት ተጠቃሚዎች ናቸው፡፡

ፕሮግራሙ ድህነትን በመቀነስ እና የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ ተደራሽ ከመሆን አንጻር ውጤት ማምጣት እንደተቻለበት ተገልጿል፡፡

በዚህም ከ3 ነጥብ 9 ሚሊየን በላይ ወገኖች በምግብ ራሳቸውን መቻላቸው ተረጋግጧል ነው የተባለው።

በፈረንጆቹ 2018 በተደረገ ዳሰሳ ሃገራዊ ድህነትን ከመቀነስ አንፃር ፕሮግራሙ ከ2 በመቶ በላይ አበርክቶ እንደነበረው ተነግሯል።

በፕሮግራሙ ማስጀመሪያ ላይ ባለድርሻ አካላት እና የዓለም አቀፍ ረጅ ሃገራት ተወካዮች ተገኝተዋል፡፡

ፕሮግራሙ ለቀጣዮቹ አምስት አመታት በተለያዩ ክልሎች የሚተገበር ይሆናል፡፡

በይስማው አደራው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.