Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ ልዩ የሆኑ 3 ሺህ ፎቶዎችን በዲጂታል መልክ ለጎብኚዎች ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 20 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ ልዩ የሆኑ 3 ሺህ ፎቶዎችን በዲጂታል መልክ ለጎብኚዎች ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ ነው።

የፎቶግራፍ ባለሙያዎች ስራዎቻቸውን ለሽያጭ ማቅረብ የሚችሉበት አሰራርም እየተዘረጋ መሆኑ ተመላክቷል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የቱሪዝም ዘርፉን ማዘመን የሚያስችላቸውን ስምምነት ፈጽመው ወደ ስራ መግባታቸው ተገልጿል።

አሰራሩ ፎቶ መግዛት የሚፈልጉ ጎብኚዎች የሚፈልጓቸውን ፎቶዎች ባለቡት ቦታ ሆነው እንዲገዙና በፈለጉት መጠን ተሰርቶ እንዲላክላቸው የሚያስችል መሆኑን ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጅ ሚኒስቴር አስታውቋል።

በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ፕሮግራም ማኔጀር አቤል ሰለሞን÷ የሀገራችን የፎቶ ግራፍ ባለሙያዎች ስራዎቻቸውን በዚህ ስርዓት ውስጥ በማስገባት ለሽያጭ የሚያቀርቡበትና ተጠቃሚ የሚሆኑበት መንገድ ይመቻቻል ብለዋል።

በኢኮሜርስ አማካኝነት ፎቶዎች ለሽያጭ  ቀርበው የውጭ ምንዛሬ ማግኘት የሚያስችል አሰራር እየተዘረጋ መሆኑንም ጠቁመዋል።

ወደ ስርዓቱ የሚገቡት ፎቶዎች መውረድ የማይችሉ፣ ባለቤት ያላቸውና ደረጃቸውን የጠበቁ ሲሆኑ ስርዓቱ ለስራ ፈጠራ፣ ለውጭ ምንዛሬ ግኝትና ቱሪዝም ለማስተዋወቅ ትልቅ ጠቀሜታ ይኖረዋልም ነው የተባለው።

ቱሪዝምን ዲጂታል ማድረግ የኢትዮጵያ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስትራቴጂ አንዱ አካል ነው።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.