Fana: At a Speed of Life!

በ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከግማሽ በላይ ተማሪዎች ከ350 በላይ አምጥተዋል

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 20 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የ2012 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከወሰዱት መካከል ከግማሽ በላይ ተማሪዎች ከ350 በላይ ማምጣታቸው ተገለፀ።
የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤትን በተመለከተ የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥቷል።
የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ዲላሞ ኦተሪ የ2012 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በተመዝጋቢ፣ በተፈታኝ እንዲሁም በውጤትም ደረጃ ከፍተኛ መሆኑን ገልፀዋል።
ፈተናውን ከወሰዱ አጠቃላይ ተፈታኞች ውስጥ 55 ነጥብ 7 በመቶዎቹ ከ350 በላይ አምጥተዋል ብለዋል።
በመግለጫው የፈተና ውጤት ካለፈው አመት ጋር ሲነፃፀር የተሻለ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በዚህም ከ600 በላይ ያመጡ ተማሪዎች 702 መሆናቸው ተገልጿል።
የዓመቱ ከፍተኛ ውጤትም 669 ሆኖ መመዝገቡን ዳይሬክተሩ ተናግረዋል ።
ተማሪዎችም በፈተናዎች ኤጀንሲ ድረገፅ እንዲሁም በአጭር የፅሁፍ መልዕክት 8181 የፈተና መለያ ቁጥራቸውን በማስገባት ከነገ ጀምሮ ውጤታቸውን መመልከት ይችላሉ ተብሏል።
ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ጊዜን እና ማለፊያ ነጥብን በተመለከተ ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ጋር እየተሰራ መሆኑም ዳይሬክተሩ በመግለጫው አስታውቀዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.