Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ ከነገ ጀምሮ የማህበር ቤት ምዝገባ ይካሄዳል

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከነገ ጀምሮ ለተከታታይ አስራ አምስት ቀናት የማህበር ቤት ምዝገባ እንደሚካሄድ የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከተማዋ የሚታየውን የመኖሪያ ቤት እጥረት ለመቅረፍ በ10/90፣ 20/80 እና 40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም ቤቶችን በመገንባት በዕጣ ለተጠቃሚዎች አስተላልፏል ፤ በቀጣይም ለባለዕድለኞች ለማስተላለፍ ቤቶችን በመገንባት ላይ ይገኛል፡፡

የነዋሪችን የመኖሪያ ቤት ፍላጎት ለመመለስ ሌሎች የቤት አማራጮችን በማመቻቸት ተጠቃሚ ለማድረግ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ሲሰራ ቆይቷል፡፡

በዚህ መሰረት ከነገ ጀምሮ በማህበር ተደራጅተው ቤት ለመገንባት አቅም እና ፍላጎት ያላቸውን ነዋሪዎች ምዝገባ እንደሚጀምር ቢሮው አስታውቋል፡፡

በመሆኑም ቀደም ሲል በ2005 ነባር በ20/80 እና በ40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም ተመዝጋቢ የሆኑ፣ቁጠባቸውን ያላቋረጡ፣በማህበር ተደራጅተው ቤት ለመስራት ፍላጎቱ ያላቸው ተመዝጋቢዎች፣ በማህበር ከተደራጁ በኋላ ከእያንዳንዱ አባል የሚጠበቀውን የቤቱን ወጪ የ70 በመቶ ክፍያ በቅድሚያ ለመክፈል ፈቃደኛ የሆኑ ተመዝጋቢዎች ወደ ቢሮ በመምጣት ሳያስፈልጋቸው በቀጥታ በቢሮው አድራሻ WWW.aahdab.gov.et አማካኝነት ከነገ ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት/ቅዳሜ እና እሁድን ጨምሮ/ ምዝገባችውን ማካሄድ እንደሚችሉ ቢሮው ገልጿል፡፡

በተጨማሪም በምዝገባ ወቅት ችግር ያጋጠማቸው ተመዝጋቢዎች ምዝገባው ከተጠናቀቀ በኋላ በቢሮ ቀርበው ማመልከት እንደሚችሉ ከአዲስ አበባ ከተማ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ነባሩ እና መደበኛው የ20/80 እና የ40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም ግንባታ ስራ በተለመደው አሰራር እንደሚቀጥልም ተገልጿል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.